ቅድስት ድንግል ማርያም

ቅድስት ድንግል ማርያም
ምስለ ፍቁር ወልዳ

Sunday, September 7, 2014

መልአከ መንክራት መምሕር ግርማ ወንድሙ በዙሪክ

በዙረክ የደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ከርስቲያን አዘጋጅነት ለሶስት ቀናት የተዘጋጀው የመላከ መንክራት መምሕር ግርማ ወንድሙ የወንጌልና የፈውስ አገልግልት በሕዝብ ብዛት  በተፈጠረ መጨናነቅ በሁለተኛው ቀን ተቕረጠ!
በሃገረ ስዊዘርላንድ በአይነቱ የመጀመርያው ነው ተብሎ የታመነው ይኽው ሃይማኖታዊ ጉባኤ የተዘጋጀበት አዳራሽ ከተፈቀደለት 2800 ሰዎች ሶስት እጥፍ በላይ ማስተናገዱ አደገኛ ሊሆን ይችላል ተብሎ ስለታመነና በየሰዓቱ የሕዝቡ ቆጥር አካባቢው ሊያስተናግደው ከሚችለው በላይ አየሆነ በመሄዱ ምኣመኑን ይቅርታ ጠይቆ ተበትኗል::
አዘጋጁ ኮሚቴ በተፈጠረው መጨናነቅ ሃዘኑን እየገለጸ በሌላ በ ኩል ምእመኑ ለመልአከ መንክራት መምሕር ግረማ ያለውንም ክብርና ፍቅር የተገነዘበበት አጋጣሚ  በመሆኑ ለቅጣይ ዝግጅቱ ጠቃሚ ልምድ ማግኘቱ ግልጽ ነው:: አንደ ፖሊስ ገለጻ ከሆነ መግባት ክቻሉት ሌላ አካባቢው ከ5000 ባላነሱ ሰዎች ተጥለቅልቆ መዋሉን በአለታዊ ረፖርቱ ዘግቧል::
አዘጋጅ ኮሚቴው በተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት ልባዊ ሃዘኑን ለሚመለከታቸው ሁሉ አየገለጸ በቅረቡ በተሻለ ዝግጅት ተወዳጁ መምሕር ግርማን በድጋሚ የጀመሩትን የፈውስ እገልግሎት አንዲቀጥሉ ያቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለዋል:: ስለሆነም ከተገኘው ልምድ ተነስቶ የተሻለና የሕዝቡን ፍላጎት የሚመጥን ዝግጅት ክአሁኑ ለመጀመር ተወስኗል::
በዚህ አጋጣሚ በተፈጠረው አለመመቻቸት አዘጋጅ ኮሚቴው የሚመለከታቸውን ሁሉልባዊ ይቅርታ ይጠይቃል::

Monday, August 25, 2014

በመልአከ መንክራት መምሕር ግርማ ወንድሙ መንፈሳዊ አገልግሎት ላይ ለመሳተፍ ወደ ዙሪክ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ለሚመጡ ምእመናን በቅናሽ የተዘጋጀ ሆቴል! / Accomodation information Hosteling Internation Zürich

 
Accomodation information Hosteling Internation Zürich
 

For further information visit http://www.youthhostel.ch/de/hostels/zurich or contact Nathnael Ashenafi.
 
We look forward for your final booking.
 
Best regards
 
Nathnael Ashenafi
Front Office Manager
 
Youthhostel Zurich
Mutschellenstrasse 114
8038 Zürich
Tel: +41 43 399 78 00
Mobile +41 79 935 92 32
Fax: +41 43 399 78 01

Saturday, August 23, 2014


Wednesday, August 20, 2014

Monday, August 18, 2014

የመልአከ መንክራት መምሕር ግርማን የፈውስ አገልግሎት ሸታችሁ ወደ ዙሪክ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለምትመጡ

የመልአከ መንክራት መምሕር ግርማን የፈውስ አገልግሎት ሸታችሁ ወደ ዙሪክ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከ ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜ 2 ቀን (05.09.2014 - 07.09.2014) ድረስ የሚከተሉት ሆቴሎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ጥሩ አገልግሎት ያላቸው መሆኑን አረጋግጠን መርጠናል።  አድራሻዎቹን ከእነ ድረ ገጾቹ ከሰር ያገኑዋቸዋል።

 
Hostel Krone Zürich
Hostels, Youthhostel, Jugendherberge
Limmatquai 88
8001 Zürich
Tel.044 260 11 70 *
E-Mailbooking@hostel-zurich.com


lbis City West Hotel - GalaHotels.com‎

Adibis-citywest-zurich.galahotels.com/
+44 20 3384 6448
 
 
Hotel Belair
Alte Winterthurerstrasse 16,
 8304 Wallisellen
+4144 839 55 55
 

ተጨማሪ  አድራሻዎች እንደተገኙ እናስታውቃለን።


ታላቅ የወንጌል ትምሕርትና የፈውስ አገልግሎት በመልአከ መንክራት መምሕር ግርማ ወንድሙ፡በሰዊዘርላንድ / ሎዛንና ዙሪክ



 

Wednesday, March 5, 2014

ቅዳሴ

አሑድ የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. (9.3.2014) በደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን  አቢይ ጾምን ምክንያት በማድረግ ከመደበኛው ቀን አንደተጨማሪ ሆኖ  ቅዳሴ የተዘጋጀ መሆኑን የሰበካ ጉባኤው ለተወደዱ ምአመናን ይገልጻል::

Thursday, January 30, 2014

የአስቴርዮ ማርያም በዓለ ንግሥ በደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ኦፕፊኮን/ ዙሪክ

የዘንድሮው የአስቴርዮ ማርያም የንግሥ በዓል በዙሪኳ ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን አጅግ ደማቅ በሁነ ተዋሕዶዊ ሥነ-ሥርዓት ተክብሯል:: ተጋባዥ መምህር ጳውሎስ ምክረ ሥላሴና በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት የተከበረው ሥነ-ሥርዓት የተከበረው በ17 ጥር በወንጌለ ስብክት በ18 እለተ ዕሑድ የንግሱ በዓል የተከናወነበት እለት ነበር:: አባሪ ምስሎቹን ይመልከቱ!








Monday, January 20, 2014

ከተራ ምንድን ነው?

መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
ጥያቄ
በየዓመቱ የጥምቀት በዓል በድመቀት ይከበራል፡፡ ከበዓሉ በፊት የከተራ በዓል የሚከበርበትን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ፋይዳውን ብታብራሩልን
ዮስቲና ከአዲስ አበባ
መልሱ
ከተራ ከበበ ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡ የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላል፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥል ይውላል፡፡ የምንጮች ውኃ ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ ይገደባል፡፡
ketera 2 2“ከተራ” በመባል የሚታወቀው - ዋዜማው” ሠርግው /1981፣8/ እንደገለጹት “ከተራ” የሚለው ቃል “ከተረ ከበበ ካለው የግዕዝ ግስ የወጣ ነው፡፡ ከተራ ፍቺውም ውኃ መከተር፣ ወይም መገደብ ማለት ነው፡፡” ብለው ሲፈቱ፣ ደስታ ተከለ ወልድ /1962፣ 694/ ደግሞ የጥምቀት ዋዜማ፣ ጥር 10 የጠራ ወራጅ ውኃ የሚከተርበት ታቦትና ሰው ወደ ዠማ ወንዝ የሚወርዱበት ጊዜ” ነው በማለት ይፈቱታል፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም /1948፣ 555/ ከተረ የሚለውን ቃል በቁሙ፣ “ዘጋ፣ አቆመ፣ አገደ፣ ከለከለ፡፡” ማለት ነው ብለው ይፈቱታል፡፡ በየዓመቱ ጥር 10 ቀን የምእመናኑ አብዛኛው ሥራ ውኃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ውኃው የሚከተረው በማግሥቱ ጥር 11 ቀን የጥምቀት በዓል ስለሚከበር ለሕዝቡ መጠመቂያ እንዲሆን ነው፡፡
በየሰበካው ቦታ ተለይቶና ተከልሎ ታቦታቱ በዳስ ወይም በድንኳን የሚያድሩበት፣ የተለያዩ የውኃ አካላት ተጠርገው የሚከተሩበት ወይም ሰው ሠራሽ የግድብ ውኃ የሚበጅበት ስፍራ ‹‹ባሕረ ጥምቀት››፣ ‹‹የታቦት ማደርያ›› እየተባለ ይጠራል፡ ባሕር፡- የውኃ መሰብሰቢያ (ምእላደ ማይ፣ የውኃ መከማቻ (ምቋመ ማይ) ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ‹‹የውኃ አገር›› /መካነ ማይ፣ ዓለመ ማይ/ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በቅዱስ ላልይበላ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር እየተመላለሱ በብሕትውና እና በስብከተ ወንጌል ያገለግሉ የነበሩት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በመቐለና በመርጡለ ማርያም እየተዘዋወሩ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከዋል፡፡ በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት (1260-1275 ዓ.ም) በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (1203-1204 ዓ.ም) አሳሳቢነት የተጀመረው ሥርዐተ በዓል ተጠናክሮ እንዲቀጥል በዐዋጅ ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ ታቦታቱም በሕዝብ ጥበቃና ክብካቤ ተደርጎላቸው በየጥምቀተ ባሕሩ እንዲያድሩ ወስነዋል፡፡ የበዓሉ አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና አድማሱ ብሔራዊነትን እየያዘ መጣ፡፡
ከዐፄ ገብረ መስቀል ጀምሮ የአደባባይ በዓል የሆነው የጥምቀት በዓል በ15ኛው ክ/ዘመን በደገኛው ኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ(1426-1460 ዓ.ም) አማካኝነት ታቦታቱ ወደ ወንዝ ወርደው ዕለቱን እንዳይመለሱ፣ በዚያ ፈንታ በጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርደው እንዲያድሩ፣ አገሩን በኪደተ እግር ይባርኩም ዘንድ በሄዱበት መንገድ እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ፡፡ ይህን ታሪክ በመከተል ዐፄ ናዖድ (1486-1500) ዓ.ም) ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመን ታቦተ ሕጉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በሚወርድበት እና ከባሕረ ጥምቀቱ ወደ ቤተ መቅደሱ በሚመለስበት ጊዜ አጅቦ አውርዶ፣ አጅቦ መመለስ እንዳለበት በዐዋጅ አስነግረው ነበር፡፡ ሕዝቡም ታቦታተ ሕጉን በሆታና በእልልታ ከቤተ መቅደስ አጅቦ ከአወጣ በኋላ በባሕረ ጥምቀት ከትሞ ማደር ጀመረ ።/ሐመር ጥር/የካቲት 1998 ዓ.ም/
ketera 3ታቦታት ከአንድ በላይ ሆነው ወደ ከተራው ስለሚሄዱ እግዚአብሔር አምላክ ለነብዩ ሙሴ “የታቦት መኖር ከእናንተ ጋር የመኖሬ ምልክት ነው” ዘፀ 25÷1 እንዳለው ታቦተ ሕጉን ተሸክመው ዮርዳኖስን እንደ ተሻገሩት ካህናተ ኦሪት፤ ካህናቱ የማይለወጠውን ታቦተ ሕጉን በራሳቸው ተሸክመው የብሉዩን ሥርዓት ከሐዲስ ኪዳን ጋር አንድ አድርገው የሐዲስ ኪዳን መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስን እያሰቡ፤ ካህናተ ሐዲስም ወደ ከተራ (ዮርዳኖስ) ይጓዛሉ፡፡ ሊቃውንቱም እንዲሁ ለበዓሉ የሚስማማውን ቃለ እግዚአብሔር እያደረሱ እንደሚያድሩ ሊቀ ጠበብት ሐረገወይን አገዘ ያስረዳሉ።
ሊቀ ጠበብት አያይዘውም የከተራ ዕለት ጥር 10 ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ የሄደበትን ለማዘከር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ኃዳፌ ነፍስ ለጻድቃን የሚለውን ዋዜማ ይቆማሉ፡፡ የዋዜማው ቀለም ከቀኑ በአራት ሰዓት በመላው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ይጀመራል ከዚያም የዋዜማው ሥርዐት ቅዱስ ተብሎ እስከ ሰላም ያለው ቀለም ይደርሳል፡፡ በዕለቱም ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ ታቦተ ሕጉን የሚያነሡት ሰሞነኛ ካህን ከምግበ ሥጋ ተከልክለው ለዕለቱ የሚገባውን ጸሎት ያደርሳሉ፡፡
በከተራው ዕለት ድንኳን ተተክሎ፣ ዳሱ ተጥሎና ውኃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ታቦተ ሕጉ የሚንቀሳቀስበት ሰዓት ሲደርስ የየቤተ መቅደሱ ታቦታት በወርቅና በብር መጎናጸፊያ እየተሸፈኑ በተለያየ ኅብር በተሸለሙ የክህነት አልባሳት በደመቁ ካህናትና የመጾር መስቀል በያዙ ዲያቆናት ከብረው፣ ከቤተ መቅደስ ወደ አብሕርት /ምጥማቃት/ ለመሄድ ሲነሡ መላው አብያተ ክርስቲያናት የደወል ድምፅ ያሰማሉ፡፡ ምእመናን ከልጅ እስከ ዐዋቂ በዐጸደ ቤተ ክርስቲንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች ‘’ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ …’’ እንደሚባለው ያማረ ልብሳቸውን ለብሰው በዓሉን ያደምቃሉ፡፡
ሊቀ ጠበብት የበዓሉን ሂደት ሲገልጹ ታቦቱ ከመንበረ ክብሩ ሲነœ ‹‹ዮም ፍስሀ ኮነ›› ተብሎ ከተጸነጸለ በኋላ ታቦቱ ወጥቶ ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት የሚለው ሰላም በሊቃውንቱ ይዘመራል፣ ይጸነጸላል፣ ይመላለሳል፡፡ የወርቅ ካባና ላንቃ የለበሱ ቀሳውስት፣ መነኮሳት ጥላ የያዙት ከታቦቱ ጎን መስቀልና ጽና የያዙት ከታቦቱ ፊት ይሄዳሉ፡፡ እንደ ቀሳውስቱ ተመሳሳይ ልብሰ ተክህኖ የለበሱት ዲያቆናት ጥላ፣ መስቀልና ቃጭል ይዘው እያቃጨሉ ከቀሳውስቱ ፊት በመሆን ያጅቧቸዋል፡፡ ከነዚህም ሌላ ካባ፣ ላንቃ ጥንግ ድርብ የለበሱ መዘምራን የብር፣ የነሐስ መቋሚያና ጸናጽል ይዘው ‹‹ወረደ ወልድ›› የሚለውን አመላለስ እያሸበሸቡ ዲያቆናቱን ቀድመው ይሄዳሉ፡፡
የደብር አለቆችና አበው ካህናት ታቦቱን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችም በተለያዩ ቀለማት ባሸበረቁ አልባሳት ተውበው ትርዒት እያሳዩ “ወረደ ወልድ፣ እግዚኡ መርሐ፣ ሆረ ኢየሱስ” እና ሌሎችንም የአማርኛ መዝሙራትን እየዘመሩ፣ እናቶች “ነይ ነይ እምዬ ማርያም” እያሉ ሌሎችም ምስጋናዎችም እየቀረቡ ጉዞ በዝግታ ወደ ጥምቀተ ባሕር ይሆናል፡፡
የከተራ በዓል ማክበሪያ ቦታ እንደደረሱ ታቦታቱ በድንኳኑ አጠገብ ቆመው ‹‹ወረደ ወልድ›› የሚለው ሰላም ተመርቶ በአግባቡ ከተለዘበ በኋላ ጸሎት ተደርጎ የዕለቱ ትምህርተ ወንጌልና ዝማሬ ከቀረበ በኋላ ውዳሴ ማርያም፣ መልክዐ ኢየሱስ ተደግሞ ታቦታ ሕጉ ወደ ተዘጋጀላቸው ድንኳን ይገባሉ /ሠርግው፤ 1981፣ 9/፡፡ በሁለተኛ የአገልግሎት ክፍል ካህናቱ ስብሐተ እግዚአብሔር ሲያደርሱ ያድራሉ፡፡ በመንፈቀ ሌሊትም ሥርዐተ ቅዳሴው ተጀምሮ ከሌሊቱ በ9፡00 ሠርሆተ ሕዝብ ይሆናል፡፡ በነጋታው የሥርዐተ ጥምቀቱ መርሐ ግብር ይቀጥላል፡፡
የከተራ በዓል ምሳሌያት
በበዓለ ጥምቀት ዋዜማ የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድና የባሕረ ጥምቀቱ መዘጋጀት ሃይማኖታዊ ታሪክና ምሳሌ አለው፡፡የቃል ኪዳኑን ታቦት አክብሮ መጓዝና ወደ ወንዝ መወረድ የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ኢያሱ በሙሴ እግር ተተክቶ ሕዝበ እስራኤልን እየመራ ከዮርዳኖስ ወንዝ ሲደርስ ባሕሩ ከሁለት ይከፈልና ወራጁም ይቆም/ይከተር/ ነበር፡፡ እስራኤል ዘሥጋ ወደ ምድረ ርስት ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ ሲሻገሩ፡- ድንኳን ጥለው የቃል ኪዳኑን ታቦት በድንኳን ውስጥ አድርገው ሌዋውያኑ በዙሪያው፣ ካህናቱ ደግሞ በውስጥ ኾነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አድረው በማለዳ ተሻግረዋል /ኢያሱ 3÷8-9/፡፡ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት አክብረው የወንዙን ዳርቻ በረገጡት ጊዜ እንደ ክረምት ማዕበል ይወርድ የነበረው ውኃ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ወደ ላይ ቆሟል፡፡ ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ታቦተ ጽዮንን ያከበሩት ካህናት ከወንዙ መሀል ይቆሙ ነበር፡፡ በዚህ መሠረት ‹‹ወተጠምቃ እገሪሆሙ ለካህናት›› ይህም ‹‹የካህናት እግሮቻቸው የዮርዳኖስን ውኃ በመርገጣቸው እንደ ጥምቀት ሆናቸው›› በሐዲስ ኪዳነ ጌታችን ለመሠረተው ሥርዐተ ጥምቀት ምሳሌ ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የጥምቀትን ዋዜማ ከተራ ብላ የጠራችው ከዚህ በመነሣት ነው፡፡
ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ የላይኛው ሸሽቶ ወደ ላይ ተመልሶ ሽቅብ ፈሷል፡፡ የታቹም ወደ ታች ሸሽቷል፡፡ የላይኛው ፈሳሽ ተቋርጦ እንደ ክምር ተቆልሎ ቀርቷል።ቅዱስ ዳዊት የተመለከተውም ይህንኑ ነው። ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ቤዛነት ተቋርጦ ፤ የታቹም ፈጽሞ መድረቁ ኃጢአተ አዳም የመጥፋቱ ምሳሌ ነው፡፡ እስራኤል ፈለገ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ኢያሪኮ መሔዳቸው ምእመናን በጥምቀት ከኃጢአት ቍራኝነት ተላቀው እግራቸውን ወደ ልምላሜ ገነት ወደ ዕረፍት መንግሥተ ሰማያት አቅንተው ለመሔዳቸው ምሳሌ ነው፡፡ ኢያሱ የጌታ፣ እስራኤል የምእመናን፣ ዮርዳኖስ የጥምቀት፣ ምድረ ርስት የገነት መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው፡፡
ታቦቱን አክብሮ የሚሔደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ፣ታቦቱ የጌታችን፣ ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ፣ ታቦታቱን አጅበው የሚሔዱትና በዓሉን የሚያከብሩት ምእመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩት ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ታቦታቱ በጥምቀት ዋዜማ ከመንበራቸው ወደ ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸውና በዚያ ማደራቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተሰልፎ ተራውን ሲጠብቅ ማደሩን ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጥምቀት የሞቱና የትንሣኤው ምሳሌ ነው፡፡ ከኃጥአን ጋር ተቆጥሮ እንዲጠመቅና እንዲሰቀል የተጻፈውን ቃል ንስሐና ጥምቀት የማያስፈልገው ሲሆን ነገር ግን ፍጹም ኃጥእ መስሎ በዮሐንስ እጅ ጥምቀትን ለመፈጸም በማየ ዮርዳኖስ እግር ተጠመቀ፡፡›› /ኪ.ወ.ክ ፤517/፡፡
ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናብ፣ የበረዶ ወራት ነው፡፡ ከወንዝ ዳር ያለ መጠለያ መዋልና ማደር አይቻልም፡፡ በመኾኑም ከዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ሁሉ በዮርዳኖስ ዙሪያ ድንኳናቸውን ተክለው ያርፉ ነበር፡፡ በዚህ አንጻር ዛሬም በባሕረ ጥምቀት ዙሪያ ድንኳኖች ዳሶች ይጣላሉ፡፡

በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ በአክሱም የንግሥት ሳባ መዋኛን ‹‹ማይ ሹም›› በጎንደር የዐፄ ፋሲል መዋኛን፣ በላስታ የላሊበላ መዋኛን፣ በሸዋ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ፍርድ መስጫ አደባባይን፣ አርባ አራት ታቦታት የሚያድሩበትን የሸንኮራ ሜዳን “ራቡቴ ወንዝ” በአዲስ አበባ ደግሞ ጃንሆይ ሜዳን /ጃንሜዳን/ ወዘተ ለአብሕርተ ምጥማቃት እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡ እኒህ ቦታዎች ዛሬም ድረስ ተከብረው ይገኛሉ፡፡እኛ በዚህ ወቅት ታቦት ይዘን፣ ከወንዝ ወርደን፣ ድንኳን ተክለን በማክበራችን ይፈጸማል፡፡

ከሶደሬ ድረ ገጽ የተገኘ-

Sunday, January 19, 2014

አስተርአዮ ማርያም - መምሕር ጳውሎስ መልካአ ሥላሴ -በዙሪክ/ኦፕፊኮን ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::

የፊታችን ቅዳሜ ጥር 17 ቀንና እሑድ ጥር 18 ቀነ (Jan.25+26) በዙሪክ/ኦፕፊኮን ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊውን የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን አስተርአዮ ማርያም  ምክንያት በማድረግ ቅዳሜ 15:00 ሰዓት ላይ የሚጀምር ታላቅ የመንፈሳዊ ጉባኤ በመምሕር ጳውሎስ መልካአ ሥላሴ ይቀርባል:: እሑድ በዓለ ንግሥ በታላቅ ሥነ-ሥርአት ይከበራል:: የምሥራቹን ላልሰሙ ወገኖች አሰምታችሁ የመንፈሳዊ ትምሕርቱ ተጠቃሚዎችና የበረክቱ ተሳታፊዎች አንድትሆኑ ቤተ ክርስቲያኑቱ ጥሪ ታቀርባለች::