ቅድስት ድንግል ማርያም

ቅድስት ድንግል ማርያም
ምስለ ፍቁር ወልዳ

Friday, June 25, 2010

Abune Melketsedek verstorben


Seine Heiligkeit Abune Melketsedek, Erzbischof von Kembata, Hadiya, Gurage und Silte ist letzten Samstag verstorben.


Unter seiner Heiligkeit fand das tausendjährige Mehur Eyesus Kloster zu neuem Glanze. Er liess es ausbauen und um Bildungseinrichtungen erweitern. Zudem reiste er häufig durch Europa, um Spenden für seine unzähligen humanitären und geistlichen Projekte zu sammeln.So kam seine Heiligkeit auch mehrmals in die Schweiz und nahm auch zweimal an der Orthodoxen Vesper zu Ehren der Stadtheiligen Felix, Regula und Exuperantius in Zürich teil.


Unermüdlich setzte er sich für Waisenkinder ein, denen er ein neues Zuhause gab und ihnen eine Schulbildung ermöglichte.


Die Debre Gennet Qiddist Maryam Kirchgemeinde in Opfikon-Glattbrugg wurde von seiner Heiligkeit mehrmals mit einem Besuch beehrt, wodurch über die Jahre eine enge Verbindung zu ihm entstanden ist.

Videos:

Seine Heiligkeit besucht das St. Avgin Kloster der syrisch-orthodoxen Kirche:







Seine Heiligkeit an der Orthodoxen Vesper zu Ehren der Zürcher Stadtheiligen:












Sunday, May 9, 2010

በእሾሆች መካከል ያበበች በእውነት የሃይማኖት አበባ ናት

በማዕከለ አስዋክ ዘፀገየት ፅጌ ሃይማኖት ዘበአማን፤
በእሾሆች መካከል ያበበች በእውነት የሃይማኖት አበባ ናት፤
ቅዱስ ያሬድ፤



ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር በኃጢአት ለወደቀው አዳም የገባለት ቃል ኪዳን « ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ» የሚል እንደነበር ሁሉ ለታላቁ የሃይማኖት አባት አብርሃምም እንደዚሁ «በዘርህ አህዛብ ይበረካሉ» የሚል ቃልኪዳን ገብቶለት ነበር ዘፍ፤12፤2-3 የሐ.ስራ 3፤25 የሰጠውን ቃል ኪዳን የማያስቀር አምላክ ጊዜው ሲደርስ ፈፀመው። መቼም ፍጥረት ያለ ታሪክ ታሪክም ያለፍጥረት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፤ ስለዚህ በደግነትም ሆነ በክፋት ብዙም ሆነ ጥቂት ታሪክ የሌለው ፍጥረት የለም። ይህንን ለማለት የተፈለገው በንፅህናዋ ያለተጓዳኝ ተፈጥራ ብቻዋን የኖረች የወላደተ አምላክ ልደት እንደ እርሷ ክብር ሳይሆን በመጠኑ ለማስታወስ ተፈልጐ ነው።

ምክንያቱም ከድንግል ማርያም በቀር ማንኛውም ፍጥረት ያለ ተጓዳኝ ተፈጥሮ የኖረ የለም ያልተፈጠረው አንድ አምላክ ብቻ እንጂ፡፡ ድንግልናዋም ቢሆን ከመነገር በላይ ነው፤¸በድንግልና ፀንሶ በድንግልና ወልዶ ድንግል ሆኖ የኖረ ፍጥረት ስለማይገኝ በዚህም ብቸኛ ናት።

እንዲህ ያለችውን ያስገኙ ወላጆቿ ኢያቄምና ሐናም በጥንተ ተፈጥሮ አንድ ወንድ በአንድ ሴት በሚለው ንፁህ ጋብቻ የኖሩ፤ በእግዚአብሔር ሕግ የሚመሩ፤ በኅብረተሰባቸው ዘንድ የተከበሩ ፃድቃን እንደነበሩ በስነ ምግባር የታነፀ የሕይወት ታሪካቸው ይናገራል።
ይህን በመሰለ የህይወት ኑሮ እየኖሩ ፅድቅ የማይጠይቅ፤ ማንም ያላጣውንና ከከበረ ጋብቻቸው ማግኘት የሚገባቸውን ልጅ ሳያገኙ ብዙ ዘመናትን አሳልፈዋል። ቢሆንም ትዳራቸው እግዚአብሔር ያልተለየው በእግዚአብሔር የሚጠበቅ ሰላማዊ ነበር። እነሱም ቢሆኑ ዝም ብለው አልተቀመጡም ወደ ሚመለከተው ክፍል በንፁሕ መስዋዕትና ፀሎት መላልሰው ሲያመለክቱ ኖረዋል። በትክክል የለመኑትን የማይነሳ በእውነት የነገሩትን የማይረሳ አምላክ ከእነሱ በላይ ለእነሱ በማሰብ ትዳራቸውን ለትልቅ ነገር ሲጠብቀው ኖሮ በጊዜው ጊዜ የማንም ጋብቻ ሊያስገኛት ያልቻለውና የማይችልው የከበረች ልጅ አስረክቧቸዋል።
በመሆኑም በመዝሙረ ዳዊት « በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት ወደ አምላኬም ጮህኹ ከመቅድሱም ቃሌን ሰማኝ፤» መዝ፤17፤6 እንደተባለው ልዑል እግዚአብሔር የቅዱስ ኢያቄምና የቅድስት ሐናን ፀሎትና ልመናቸውን ተቀብሎ ለማደሪያነት የመረጣት ወላዲተ አምላክ ነሐሴ 7 ቀን ተፀንሳለች። በተፀነሰችም ጊዜ ብዙ ተዓምራት ተደርገዋል በነቢያት ዘመን ነቢዩ ኤልያስ ( 2ኛ ፤ነገ.13፤2) በዘመነ ሐዋርያት እነ ቅዱስ ጴጥሮስ የሐዋ. ሥራ 5፤15 በጥላቸው ገቢረ ተዓምራት እንደፈጸሙ ሁሉ እመቤታችንም በማህፀነ ሐና እያለች የቤርሳቤህን ዓይን አብርታለች።
የፅንሱም ወራት ከተፈጸመ በኋላ ግንቦት 1 ቀን ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ ደምግባትና መወደድ ያላት ወላዲት አምላክ ተወለደች። « ኢያቄም ወሐና ወለዱ ሰማየ ሰማዮሙኒ አስረቀት ፀሐየ» ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱ ሰማይም ፀሐይን አስገኘች(ወለደች) እንደለ ሊቁ።

እመቤታችን የተወለደችው ሊባኖስ በተባለ ተራራ ላይ ነው። በሊባኖስ ተራራ ላይ እመቤታችን እንድትወለድ ምክንያቶቹ አይሁድ ቢሆኑም ምሥጢሩ ግን የተነገረው ትንቢት እንዲፈጸም ነው።

ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ መኃ 4፤8
ሙሽሪት ሆይ ከሊባኖስ ነይ ከሊባኖስ ነይ የሚል ትንቢት ነበርና። በዚህ እለትም የመላው ዓለም የጨለማ ህይወት በብርሃን፤ ዓመተ ፍዳ ዓመት ኩነኔ በዓመተ ምህረት የሚለወጥበት ዋዜማ በመሆኑ ታላቅ ደስታ ተደርገ። ከዲያብሎስና ሠራዊቱ በስተቀር ዓለም የመልካም ዜና መጀመርያውን ቀን ሲያውቀውም ሳያውቀውም አከበረ የአምላክ እናት ተወልዳለችና።

እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማንያን የድንግል ማርያም የአሥራት ልጆች እንደመሆናችን መጠን እናታችን ቅድስት ማርያም ቤተሰቦቿ ከቤታቸው እና ከቄያቸው ተሰደው ብዙ አፀድ ባለበት በአድባረ ሊባኖስ በመወለዷ ይህንን የልደቷን ቀን በገጠር በከተማ፤ ልጅ አዋቂው፤ ሀብታምና ድሀው በአንድነት በሰፈር ውስጥ በመሰባሰብ ሁሉም ያለውን በማምጣት በጋራ በፍቅር በደስታ ያከብራሉ፤ ምንም እንኳ አንዳንዶች ይህንን ያማረ ትውፊት ለባዕድ አምልኮት ቢጠቀሙበትም ከእንዲህ ያለ ምግባረ ብልሹነት ተቆጥበን የመጀመርያውን ዓላማ ጠብቀን የዚህችን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት ቅድስት እናት በዓለ ልደት የእያንዳችን የድህነት ብስራት ቀን መሆኑን አውቀን ያለምንም ልዩነት በአንድነት፤በሰላም፤በፍቅር፤በደስታ ልናከብረውና ሃይማኖታዊ እሴቱ ሳይበላሽ፤ሳይበረዝና ሳይለቅ ለትውልድ ልናስተላልፍ ይገባል።

ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ረድኤት ይርዳን አሜን።

መልአከ ገነት
አባ ኃይለ ጊዮርጊስ ወልደ ማርያም(ቆሞስ)

ግንቦት 1 ቀን 2002 ዓ/ም

+   +   +

የዕለቱ ምስባክ
መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን
ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን
እምኩሉ ተዐይኒሁ ለያዕቆብ
መዝ፣86፣1-2

+ + +

Tuesday, March 2, 2010

ጾም ማለት የምግብ ለውጥ ማድረግ ብቻ ነውን?

በዚህ በጀመርነው የአቢይ ጾም ወቅት ለጿሚው አዳጋች የሚባለው "የጾም ምግብ" በቀላሉ አለማግኘት ነው ይባላል:: ብዙዎች አሣም ደም አለውና አይበላም ይላሉ:: የጾሙ ከፍስኩ እንዳይነካካ ብርቱ ጥንቃቄ የሚያደርጉም ጿሚዎች ቁጥር የሚናቅ አይደለም:: በዚህ በስደት ዓለሙም ቢሆን በተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ከተደነገጉት ሰባቱ አጽዋማት መካከል የአቢይ / ሁዳዴ ጾምን አብዛኛዎቹ አማንያን ይጾሙታል:: የምግብ ለውጥ ይደረጋል ማለት ነው::
ምንም እንኳን ቀን እየተቆጠረ ዛሬ ጾም ስለሆነ ልጠንቀቅ ነገ እፈስካለሁ የሚባል ባይሆንም በተለይ በዚህ ወቅት ልንጾማቸው (ልንታቀብ) የሚገባን ሌሎች ነገሮች ያሉ አይመስሏችሁም?

ሀሜት - ምቀኝነት -ቅናት -ተንኮል -ሸር - ሃሰተኝነት.ወዘተ ከሥጋውና ከቅቤው የበለጠ አያረክሱም? በእርግጥ የባህርይ ለውጥን የሚጠይቅ ቢሆንም ወደ አፍ ከሚገባው ባልተናነሰ ሁኔታ ከአፍ የሚወጣውን መጠንቀቁም ሊዘነጋ የማይገባው የጾም አይነት ይመስለኛል::በዚህ ጉዳይ ላይ በሰፊው እመለስበታለሁ::ጾሙን የሰላም የመፈቃቀር የመተሳሰብና ከእኛ ባነሰ ሁኔታ የሚኖሩትንም የምናስብበት ወቅት ያድርግልን:: ሀገራችን ኢትዮጵያን አምላክ ይጠብቅልን! አሜን::