Tuesday, May 8, 2012
የግንቦት ልደታ አከባበር - ከምስል ማሕደራችን
Monday, May 7, 2012
የልደታ በዓል እጅግ ደማቅ በሆነ ሥነ-ሥርዓት ተከበረ!
የእመቤታችን የድንግል ማርያም የልደት በዓል (ግንቦት ልደታ) እሁድ ሚያዝያ 28 ቀን 2004 ዓ.ም. በዙሪክ የደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀትና ንግሥ ተከበረ:: ክተለያዩ የስዊስ ካንቶኖችና አጎራባች አገሮች በተሰበሰቡ ምእመናን በተዋሕዷዊ መዝሙሮችና ያሬዳዊ ወረቦች ያማረውን አከባበር የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በዚህ ገጽ ላይ ይቀርባል::
"ከሺ ቃላት አንድ ምስል በይበልጥ ይገልጻል " ነውና ምስሎችን ይመልከቱ:: (ፎቶዎች በተስፉ ወልደ ሥላሴ)
"ከሺ ቃላት አንድ ምስል በይበልጥ ይገልጻል " ነውና ምስሎችን ይመልከቱ:: (ፎቶዎች በተስፉ ወልደ ሥላሴ)
Thursday, May 3, 2012
የግንቦት ልደታ የንግሥ ሥነ-ሥርዓት በኦፕፊኮን ደብረ ገነት ቅ.ማርያም ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ይከበራል!
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::
በዙሪክ/ኦፕፊኮን (ስዊዘርላንድ)የደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የዘንድሮውን የግንቦት ልደታን የምታከብረው ዕሑድ ሚያዝያ 28 ቀን 2004 ዓ.ም.(06.05.2012) ነው::
እንደተለመደው ሁሉ ለበዓሉ ተስማሚ በሆኑ ያሬዳዊ ዜማዎች: ቅዳሴና ንግሥ የሚከበር ሲሆን ከቅዳሴ በኋላ የእመቤታችንን ልደት ለማስታወስ ጸበል ጸዲቅ ለየት ባለ መልኩ መናፈሻ ውስጥ የሚደረግ መሆኑን የመስተንግዶ ክፍሉ አስታውቋል::
በስዊዘርላንድና አካባቢው ነዋሪ የሆኑ የተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ሁሉ በዚህ እለተ ሰንበት በመገኝት የበረከቱ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ቤተ ክርስቲያኒቱ ጥሪዋን ታቀርባለች::
Subscribe to:
Posts (Atom)